Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 24:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ከዚ​ህም በኋላ መጻ​ሕ​ፍ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ተ​ውሉ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ከፈ​ተ​ላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 በዚህ ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አእምሯቸውን ከፈተላቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ከዚህ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማስተዋል እንዲችሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 24:45
13 Cross References  

በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቀይ ሐር የም​ት​ሸጥ ከት​ያ​ጥ​ሮን ሀገር የመ​ጣች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ዋን ከፍ​ቶ​ላት ነበ​ርና ጳው​ሎስ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን ታዳ​ምጥ ነበር፤ ስም​ዋም ልድያ ይባል ነበር።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደን​ቆ​ሮስ፥ የሚ​ያ​ይስ፥ ዕው​ርስ የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?


በዚ​ያን ጊዜ የሰ​ዎ​ችን ማስ​ተ​ዋል ይከ​ፍ​ታል፥ ግርማ ባለው ራእ​ይም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋል፤


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements