Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በወ​ሰ​ዱ​ትም ጊዜ የቀ​ሬና ሰው ስም​ዖ​ንን ከዱር ሲመ​ለስ ያዙት፤ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱ​ስም በስ​ተ​ኋላ መስ​ቀ​ሉን አሸ​ከ​ሙት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኢየሱስንም ይዘው ሲወስዱት፣ ስምዖን የተባለውን የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ አግኝተው መስቀሉን አሸክመው ኢየሱስን ተከትሎ እንዲሄድ አስገደዱት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በወሰዱትም ጊዜ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ከገጠር ሲመጣ አግኝተው ያዙትና መስቀሉን ጭነውበት ከኢየሱስ በኋላ እንዲሄድ አደረጉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ ኢየሱስን ወሰዱት፤ ይዘውት ሲሄዱ ሳሉም የቀሬና ሰው የሆነውን ስምዖንን ከገጠር ወደ ከተማ ሲገባ አገኙት፤ እርሱን ይዘው የኢየሱስን መስቀል አሸከሙትና ኢየሱስን እንዲከተል አደረጉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በወሰዱትም ጊዜ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ከገጠር ሲመጣ ይዘው ከኢየሱስ በኋላ መስቀሉን እንዲሸከም ጫኑበት።

See the chapter Copy




ሉቃስ 23:26
11 Cross References  

የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።


በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ፊት አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ጸል​የ​ውም እጃ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ ጫኑ።


በፍ​ር​ግያ፥ በጵ​ን​ፍ​ልያ፥ በግ​ብፅ፥ በሊ​ብያ አው​ራጃ፥ በቀ​ር​ኔን የም​ን​ኖር፥ ከሮ​ሜም የመ​ጣን አይ​ሁድ፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም፥


መስ​ቀ​ሉን ተሸ​ክሞ ሊከ​ተ​ለኝ የማ​ይ​መጣ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።”


ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሊከ​ተ​ለኝ የሚ​ወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክ​ኖም የሞ​ቱን መስ​ቀል ይሸ​ከም፤ ዕለት ዕለ​ትም ይከ​ተ​ለኝ።


በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ።


ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements