Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 22:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 ዘወ​ት​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር በቤተ መቅ​ደስ ስኖር እጃ​ች​ሁን እንኳ አል​ዘ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን ጊዜ​ያ​ችሁ ይህ ነው፤ የጨ​ለ​ማው አበ​ጋ​ዝም ሥል​ጣኑ ይህ ነው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ከእናንተ ጋራ በነበርሁ ጊዜ እጃችሁን አላነሣችሁብኝም፤ ይህ ግን ጨለማ የነገሠበት ጊዜያችሁ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 ዕለት ዕለት ከእናንተ ጋር በመቅደስ ስሆን እጆቻችሁን አልዘረጋችሁብኝም፤ ሆኖም ይህ የእናንተ ጊዜና ጨለማው የሚሰፍንበት ወቅት ነው፤” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 በየቀኑ በቤተ መቅደስ ከእናንተ ጋር ስገኝ አልያዛችሁኝም ነበር፤ አሁን ግን የእናንተ ጊዜና የጨለማው ሥልጣን ጊዜ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 በመቅደስ ዕለት ዕለት ከእናንተ ጋር ስሆን እጆቻችሁን አልዘረጋችሁብኝም፤ ይህ ግን ጊዜያችሁና የጨለማው ሥልጣን ነው አላቸው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 22:53
20 Cross References  

ሰል​ፋ​ችሁ፦ ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


ከጨ​ለማ አገ​ዛዝ አዳ​ነን፤ ወደ ተወ​ደ​ደው ልጁ መን​ግ​ሥ​ትም መለ​ሰን።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ና​ንተ ጋር ብዙ አል​ና​ገ​ርም፤ የዚህ ዓለም ገዢ ይመ​ጣ​ልና፤ በእ​ኔም ላይ ምንም አያ​ገ​ኝም።


ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊይ​ዙት ወደ እርሱ የመ​ጡ​ትን የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችን፥ የቤተ መቅ​ደስ ሹሞ​ች​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሌባን እን​ደ​ም​ት​ይዙ በሰ​ይ​ፍና በጎ​መድ ልት​ይ​ዙኝ መጣ​ች​ሁን?


ይዘ​ውም ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ቤት ወሰ​ዱት፤ ጴጥ​ሮ​ስም ከሩቅ ይከ​ተ​ለው ነበር።


ይሁ​ዳም ያን እን​ጀራ ተቀ​ብሎ ወዲ​ያ​ውኑ ወጣ፥ ሌሊ​ትም ነበር።።


Follow us:

Advertisements


Advertisements