ሉቃስ 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 የመከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባሮቹ፥ ከወይኑ ፍሬ ይልኩለት ዘንድ አገልጋዩን ላከ፤ ገባሮቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን ሰደዱት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በመከርም ወራት፣ ከወይኑ ፍሬ እንዲልኩለት ባሪያውን ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን ባሪያውን ደብድበው ባዶ እጁን ሰደዱት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጊዜውም ሲደርስ ከወይኑ አትክልት ፍሬ እንዲሰጡት አንድ አገልጋይ ወደ ተከራዮቹ ላከ፤ ጠባቂዎቹ ግን ደበደቡትና ባዶ እጁን ሰደዱት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ወይኑ ባፈራ ጊዜ የወይኑ ተክል ባለቤት ከፍሬው ድርሻውን እንዲቀበልለት አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው፥ ባዶ እጁን ሰደዱት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 በጊዜውም ከወይኑ አትክልት ፍሬ እንዲሰጡት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎች ላከ፤ ገበሬዎቹ ግን ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት። See the chapter |