Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 2:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤተ መቅ​ደስ በሊ​ቃ​ው​ንት መካ​ከል ተቀ​ምጦ ሲሰ​ማ​ቸ​ውና ሲጠ​ይ​ቃ​ቸው አገ​ኙት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከሦስት ቀንም በኋላ፣ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያደምጣቸውና ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ እየሰማቸውና እየጠየቃቸው በመቅደስ አገኙት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ከሦስት ቀንም በኋላ በቤተ መቅደስ አገኙት፤ በዚያም በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ጥያቄም ሲያቀርብላቸው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 2:46
13 Cross References  

ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።


በሸ​ን​ጎ​ዉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የከ​በረ የኦ​ሪት መም​ህር ስሙን ገማ​ል​ያል የሚ​ሉት አንድ ፈሪ​ሳዊ ተነሣ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ከጉ​ባ​ኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው አዘዘ።


የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።


ንጉ​ሡም፥ “በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” ብሎ እንደ ተና​ገረ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ሕዝቡ ሁሉ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሮብ​ዓም መጡ።


እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሄዱ።


ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አስ​ተ​ዋ​ይ​ነ​ቱ​ንና አመ​ላ​ለ​ሱን ያደ​ንቁ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መም​ህ​ራ​ቸው ነህ፤ ነገር ግን እን​ዴት ይህን አታ​ው​ቅም?” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements