Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 2:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሕፃኑም አደገ ጠነከረም፤ ጥበብም ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ ሄደ፤ በጥበብም የተሞላ ሆነ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ ከእርሱ ጋር ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 2:40
17 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ፥ በሰ​ውም ዘንድ፥ በጥ​በ​ብና በአ​ካል በሞ​ገ​ስም አደገ።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ውም ፊት ሞገስ እያ​ገኘ ሄደ።


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አስ​ተ​ዋ​ይ​ነ​ቱ​ንና አመ​ላ​ለ​ሱን ያደ​ንቁ ነበር።


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


ሴቲ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሶም​ሶን ብላ ጠራ​ችው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው፤ ልጁም አደገ።


እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


ሐዋ​ር​ያ​ትም የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ትን​ሣኤ በታ​ላቅ ኀይል ይመ​ሰ​ክሩ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ዘንድ ታላቅ ጸጋ ነበ​ራ​ቸው።


ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥ ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፥ ሦስት ወን​ዶ​ችና ሁለት ሴቶች ልጆ​ችን ወለ​ደች። ብላ​ቴ​ናው ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አደገ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements