ሉቃስ 19:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)44 አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም44 አንቺንና በቅጥርሽ ውስጥ የሚኖሩትንም ልጆችሽን ከዐፈር ይደባልቃሉ፤ ድንጋይም በድንጋይ ላይ አይተዉም፤ የመጐብኛሽን ጊዜ አላወቅሽምና።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)44 አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም44 አንቺንና በውስጥሽ ያሉትንም ልጆችሽን በመሬት ላይ ጥለው ያወድማሉ፤ ሳይፈርስ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ በቦታው አይተዉልሽም፤ ይህም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር አንቺን ሊያድን የመጣበትን ጊዜ ባለማወቅሽ ነው።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)44 አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና። See the chapter |