Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 19:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከብበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጠላቶችሽም በዙርያሽ ቅጥር የሚሠሩበት፥ አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁብት ቀኖች ይመጣሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 19:43
15 Cross References  

እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤


በው​ስ​ጧም የሚ​ዋ​ጉ​በት ግን​ብን ሥራ፤ በሠ​ራ​ዊ​ትም ክበ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ጦር አስ​ፍር፤ የሚ​ዋጋ ጦር​ንም ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ላክ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ወደ​ዚች ከተማ አይ​መ​ጣም፤ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ አያ​ጥ​ራ​ት​ምም።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


ታናሽ ከተማ ነበ​ረች፥ ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችም ነበ​ሩ​ባት፤ ታላቅ ንጉ​ሥም መጣ​ባት፥ ከበ​ባ​ትም፥ ታላቅ ግን​ብ​ንም ሠራ​ባት።


እን​ዲ​ህም አላት፥ “አን​ቺስ ብታ​ውቂ ሰላ​ምሽ ዛሬ ነበረ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን ከዐ​ይ​ኖ​ችሽ ተሰ​ወረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements