Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 19:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በደ​ረሰ ጊዜም ከተ​ማ​ዪ​ቱን አይቶ አለ​ቀ​ሰ​ላት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ፥ ከተማይቱን በተመለከተ ጊዜ፥ አለቀሰላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥

See the chapter Copy




ሉቃስ 19:41
14 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ባ​ውን አፈ​ሰሰ።


እኔም አን​ተን ተከ​ትዬ አል​ደ​ከ​ም​ሁም፥ የሰ​ው​ንም ቀን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ከከ​ን​ፈሬ የወ​ጣ​ውም በፊ​ትህ ነው።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


እስ​ኪ​ያ​ፍ​ርም ድረስ ትኩር ብሎ ፊቱን ተመ​ለ​ከ​ተው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው አለ​ቀሰ።


ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በኃ​ጥ​ኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነ​ሣል፤ በገ​ባ​ዖን ሸለ​ቆም ይኖ​ራል፤ ሥራ​ውን ማለት መራራ ሥራ​ውን በቍጣ ይሠ​ራል፤ ቍጣ​ውም ድን​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ መር​ዙም ልዩ ነው።


እን​ዲ​ህም አላት፥ “አን​ቺስ ብታ​ውቂ ሰላ​ምሽ ዛሬ ነበረ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን ከዐ​ይ​ኖ​ችሽ ተሰ​ወረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements