Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 19:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ደብረ ዘይት ወደ​ሚ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ወዳ​ሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታ​ንያ በቀ​ረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ላከ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ወደሚገኙት፣ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ ከተሞች በቀረበ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ደብረዘይት በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበም ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወደሚገኙት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና፦

See the chapter Copy




ሉቃስ 19:29
11 Cross References  

ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ።


ከዚ​ህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚ​ባ​ለው ተራራ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሰ​ን​በት መን​ገድ ያህል የራቀ ነው።


በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፣ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፣ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል።


እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።


ወጥ​ቶም እን​ዳ​ስ​ለ​መ​ደው ይጸ​ልይ ዘንድ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ተከ​ተ​ሉት።


ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር።


ወደ ደብረ ዘይት ዐቀ​በት መው​ረ​ጃም በደ​ረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በታ​ላቅ ቃል ያመ​ሰ​ግ​ኑት ዘንድ ጀመሩ።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በፊ​ታ​ችሁ ወደ አለ​ችው መን​ደር ሂዱ፤ ገብ​ታ​ች​ሁም ሰው ያል​ተ​ቀ​መ​ጠ​በት የታ​ሰረ ውር​ንጫ ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ፈት​ታ​ች​ሁም አም​ጡ​ልኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements