Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 18:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የሚ​መ​ሩ​ትም ዝም እን​ዲል ገሠ​ጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከፊት የሚሄዱ ሰዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ፤” እያለ አብዝቶ ጮኸ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 18:39
16 Cross References  

በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ንሁ።


ይባ​ር​ካ​ቸ​ውም ዘንድ ሕፃ​ና​ትን ወደ እርሱ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አይ​ተው ገሠ​ጹ​አ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ከእኔ ያር​ቀው ዘንድ ጌታ​ዬን ሦስት ጊዜ ማለ​ድ​ሁት።


ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በሕ​ዝቡ መካ​ከል፥ “መም​ህር ሆይ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ገሥ​ጻ​ቸው” ያሉት ነበሩ።


ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።


ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው።


እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው።


“ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል።


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቆመና ወደ እርሱ እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements