Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 17:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ፈሪሳውያን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እንደምትመጣ ኢየሱስን በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት በሚታዩ ምልክቶች አትመጣም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ፈሪሳውያንም “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ “የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ፈሪሳውያን ኢየሱስን፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ሲሉ ጠየቁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት የምትመጣው ሰዎች ነቅተው በሚጠባበቁት ዐይነት አይደለም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 17:20
9 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ይህ​ንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገ​ራ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቦ ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወዲ​ያ​ውኑ የም​ት​ገ​ለጥ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።


“ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል።


ከከ​ተ​ማ​ችሁ የተ​ጣ​በ​ቀ​ብ​ንን ትቢያ እን​ኳን እና​ራ​ግ​ፍ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ እንደ ቀረ​በች ይህን ዕወቁ።


መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements