Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወደ አን​ዲት መን​ደ​ርም ሲገባ ለምጽ የያ​ዛ​ቸው ዐሥር ሰዎች ተቀ​በ​ሉ​ትና ራቅ ብለው ቆሙ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወደ አንድ መንደር እንደ ገባም ለምጽ የያዛቸው ዐሥር ሰዎች አገኙት፤ እነርሱም በርቀት ቆመው፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት ዐሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወደ አንዲት መንደርም በገባ ጊዜ ዐሥር ለምጻሞች ወደ እርሱ መጥተው በሩቅ ቆሙ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 17:12
9 Cross References  

በአ​ን​ዲት ከተማ ሳለም ሁለ​መ​ናው ለም​ጻም የሆነ ሰው መጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ በፊቱ ወድቆ ሰገ​ደ​ለ​ትና፥ “አቤቱ ብት​ወ​ድስ ልታ​ነ​ጻኝ ትች​ላ​ለህ” እያለ ማለ​ደው።


ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ።


በከ​ተ​ማ​ዋም በር አራት ለም​ጻ​ሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እስ​ክ​ን​ሞት ድረስ በዚህ ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን?


ነገር ግን የን​ዕ​ማን ለምጽ በአ​ን​ተና በዘ​ርህ ላይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ” አለው። እንደ በረ​ዶም ለም​ጻም ሆኖ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።


ዳግ​መ​ኛም፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ መልስ” አለው። እጁ​ንም ወደ ብብቱ መለ​ሳት፤ “እጅ​ህን ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ ተመ​ል​ሳም ገላ​ውን መሰ​ለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements