Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 15:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ነገር ግን ይህ ወን​ድ​ምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤ​ትም ልና​ደ​ርግ ይገ​ባል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይህ ወንድምህ ግን ሞቶ ነበር፤ ሕያው ሆነ፤ ጠፍቶ ነበር ተገኘ፤ ስለዚህ ደስ ሊለንና ፍሥሓ ልናደርግ ይገባናል።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር፤ ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል’።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህ ወንድምህ ግን ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ አሁን ተገኘ፤ ስለዚህ በጣም ልንደሰት ይገባናል።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 15:32
13 Cross References  

ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


እኔስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ለመ​ለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ታመ​ንሁ።


መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት።


አባ​ቱም እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ አን​ተማ እኮ ዘወ​ትር ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው።


የእ​ነ​ርሱ መው​ጣት ለዓ​ለም ዕርቅ ከሆነ ይል​ቁ​ንም መመ​ለ​ሳ​ቸው ምን ይሆን? ከሙ​ታን በመ​ነ​ሣት የሚ​ገኝ ሕይ​ወት ነው።


የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements