Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ በእግዚአብሔር መላእክት ዘንድ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 15:10
23 Cross References  

እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ከማ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ከዘ​ጠና ዘጠኙ ጻድ​ቃን ይልቅ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በሰ​ማ​ያት ፍጹም ደስታ ይሆ​ናል።


ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተብሎ የሚ​ደ​ረግ ኀዘን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ያ​ሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚ​ደ​ረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመ​ጣል።


እኔ ሕያው ነኝና ኀጢ​አ​ተ​ኛው ከመ​ን​ገዱ ተመ​ልሶ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢ​አ​ተ​ኛው ይሞት ዘንድ አል​ፈ​ቅ​ድም፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ተመ​ለሱ፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ? በላ​ቸው።


በውኑ ኀጢ​አ​ተኛ ይሞት ዘንድ መፍ​ቀ​ድን እፈ​ቅ​ዳ​ለ​ሁን? ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለ​ስና በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ ነው እንጂ።


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።


የም​ዋ​ቹን ሞት አል​ፈ​ቅ​ድ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስለ​ዚህ በን​ስሓ ተመ​ለ​ሱና በሕ​ይ​ወት ኑሩ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ሕ​ዛብ ደግሞ ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ንስ​ሓን ሰጣ​ቸው እንጃ” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


ስለ​ዚ​ህም እል​ሃ​ለሁ፤ ብዙ ኀጢ​ኣቷ ተሰ​ር​ዮ​ላ​ታል፤ በብዙ ወድ​ዳ​ለ​ችና፤ ጥቂት የሚ​ወ​ድድ ጥቂት ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ ብዙ የሚ​ወ​ድ​ድም ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።”


“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ግን በሌ​ሊት የወ​ኅኒ ቤቱን ደጃፍ ከፍቶ አወ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው።


ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤


“እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ።


በሰው ፊት የሚ​ክ​ደ​ኝን ግን እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት እክ​ደ​ዋ​ለሁ።


ያገ​ኘ​ቻት እንደ ሆነም ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋን ጠርታ፦ ‘የጠ​ፋ​ች​ኝን ድሪ​ሜን አግ​ኝ​ቼ​አ​ታ​ለ​ሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ’ ትላ​ቸ​ዋ​ለች።


ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበ​ሩት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements