Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 13:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱና ያችን ቀበሮ እን​ዲህ በሉ​አት፤ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋ​ን​ን​ትን አወ​ጣ​ለሁ፤ ሕይ​ወ​ት​ንም አድ​ላ​ለሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፣ እነሆ፤ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ ሕመምተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ከግቤ እደርሳለሁ ብሏል በሉት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እንዲህም አላቸው “ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ ‘እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን እፈጽማለሁ’ በሉአት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፦ ‘ዛሬና ነገ አጋንንትን አስወጣለሁ፤ በሽተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛው ቀንም ሥራዬን እጨርሳለሁ’ ይላል በሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እንዲህም አላቸው፦ ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ፦ እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፥ በሦስተኛውም ቀን እፈጸማለሁ በሉአት።

See the chapter Copy




ሉቃስ 13:32
16 Cross References  

ብዙ ልጆ​ችን ወደ ክብር ሲያ​መጣ የመ​ዳ​ና​ቸ​ውን ራስ በመ​ከራ ይፈ​ጽም ዘንድ ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ሁሉ በእጁ ለተ​ያዘ፥ በእ​ር​ሱም ሁሉ ለሆነ ለእ​ርሱ ተገ​ብ​ቶ​ታ​ልና።


ከተ​ፈ​ጸ​መም በኋላ ለሚ​ታ​ዘ​ዝ​ለት ሁሉ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኅን ሆነ።


ኦሪ​ትስ የሚ​ሞት ሰውን ሊቀ ካህ​ናት አድ​ርጋ ትሾ​ማ​ለች፤ ከኦ​ሪት በኋላ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ሐላ ቃሉ ግን ዘለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ለ​ወጥ ፍጹም ወል​ድን ካህን አድ​ርጎ ሾመ​ልን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከአ​ባቴ ብዙ መል​ካም ሥራ አሳ​የ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ነ​ርሱ በየ​ት​ኛው ሥራ ምክ​ን​ያት ትወ​ግ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ?”


ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህም ኀይል በእርሱ ይደረጋል፤” አለ።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! ነቢ​ያ​ትህ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ቀበ​ሮ​ዎች ናቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሆም​ጣ​ጤ​ውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈ​ጸመ” አለ፤ ራሱ​ንም አዘ​ን​ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።


የወ​ይን ቦታ​ችን ያብብ ዘንድ፥ የወ​ይ​ና​ች​ንን ቦታ የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን ጥቃ​ቅ​ኑን ቀበ​ሮች አጥ​ም​ዳ​ችሁ ያዙ​ልን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements