Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይህን በተናገረ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ ዐፈሩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ግን እርሱ ባደረገው ድንቅ ሥራ ሁሉ ደስ አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ይህንንም ሲናገር የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ በእርሱም በተደረጉት ድንቅ ነገሮች ሁሉ ሕዝቡ በሙሉ ደስ አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዚህም ንግግሩ ኢየሱስ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ አሳፈራቸው፤ ሕዝቡ ግን ኢየሱስ ባደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ተደሰተ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 13:17
19 Cross References  

በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።


ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።


እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።


ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ ማንም የለም።


ነገር ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትም​ህ​ር​ቱን በመ​ስ​ማት ይመ​ሰጡ ነበ​ርና።


በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።


ስለ​ዚ​ህም ነገር ሊመ​ል​ሱ​ለት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።


ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።


ክብ​ርና ባለ​ጠ​ግ​ነት በቤቱ ነው፥ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


አቤቱ፦ በአ​ማ​ል​ክት መካ​ከል አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? በቅ​ዱ​ሳ​ንም ዘንድ እንደ አንተ የከ​በረ ማን ነው? በም​ስ​ጋና የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህ፤ ድን​ቅ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ነህ፤


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements