Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 12:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ነገር ግን ይህን ሳያውቅ ቀርቶ መገረፍ የሚገባውን ያህል ያደረገ አገልጋይ በጥቂቱ ይገረፋል። ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራ ከተቀበለም ብዙ ይጠበቅበታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 12:48
21 Cross References  

ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፤ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።


“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥


ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም።


ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ል​ፎ​ታል፤ ዛሬ ግን በመ​ላው ዓለም ንስሓ እን​ዲ​ገቡ ሰውን ሁሉ አዝ​ዞ​አል።


ጌታ​ውም ጠርቶ፦ ‘በአ​ንተ ላይ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር ምን​ድን ነው? እን​ግ​ዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልት​ሆን አት​ች​ል​ምና የመ​ጋ​ቢ​ነ​ት​ህን ሂሳብ አስ​ረ​ክ​በኝ’ አለው።


ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤


በዘመኑም ጊዜ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤


“አንድ ሰው ሳያ​ውቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢ​አት አን​ዲት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ፍየል ያቀ​ር​ባል።


በደ​ለ​ኛ​ውም መገ​ረፍ ቢገ​ባው እን​ዲ​ገ​ረፍ ፈራጁ በፊቱ በም​ድር ላይ ያጋ​ድ​መው፤ የግ​ር​ፋ​ቱም ቍጥር እንደ ኀጢ​አቱ መጠን ይሁን።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ ይህን ምሳሌ የም​ት​ና​ገ​ረው ለእኛ ነውን? ወይስ ለሁሉ ነው?” አለው።


“በም​ድር ላይ እሳ​ትን አም​ጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ን​ደድ በቀር ምን እሻ​ለሁ?


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements