Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 12:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 “ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “በዐጭር ታጥቃችሁ ተዘጋጁ፤ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 “ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ባጭር ታጥቃችሁ ሁልጊዜ ለሥራ ተዘጋጁ፤ መብራታችሁም የበራ ይሁን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 12:35
11 Cross References  

ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ።


መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።


አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙ​ምም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ አይ​ተ​ኙም፤ የወ​ገ​ባ​ቸ​ውን መታ​ጠ​ቂያ አይ​ፈ​ቱም፤ የጫ​ማ​ቸ​ውም ማዘ​ቢያ አይ​በ​ጠ​ስም።


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።


እና​ን​ተም፥ በመ​ጣና በር በመታ ጊዜ ወዲ​ያው ይከ​ፍ​ቱ​ለት ዘንድ ከሰ​ርግ እስ​ኪ​መ​ለስ ጌታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ሰዎች ሁኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements