Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 11:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 እር​ሱም እን​ዲህ አለው፤ “ለእ​ና​ንተ ለሕግ ዐዋ​ቂ​ዎች ወዮ​ላ​ችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸ​ክ​ሙ​ታ​ላ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን ያን ሸክም በአ​ን​ዲት ጣታ​ችሁ እን​ኳን አት​ነ​ኩ​ትም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሕግ ዐዋቂዎችም ደግሞ ወዮላችሁ፤ ሰዎች ሊሸከሙ የማይችሉትን ከባድ ሸክም ታሸክማላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 እርሱም እንዲህ አለ፦ እናንተ ሕግ አዋቂዎች ደግሞ ወዮላችሁ! ለመሸከም ከባድ የሆነውን ሸክም ሰዎችን ታሸክማላችሁ፥ ራሳችሁ ግን በአንዲት ጣታችሁ እንኳ ሸክሙን አትነኩትምና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተም የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! በሰው ላይ ከባድ ሸክም ትጭናላችሁ፤ እናንተ ግን ሸክሙን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 እርሱም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ ሕግ አዋቂዎች፥ አስቸጋሪ ሸክም ለሰዎች ስለምታሸክሙ፥ ራሳችሁም በአንዲት ጣታችሁ ስንኳ ሸክሙን ስለማትነኩት፥ ወዮላችሁ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 11:46
7 Cross References  

እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም።


ክፉ​ንም ጽሕ​ፈት ለሚ​ጽፉ ወዮ​ላ​ቸው!


ከሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ችም አንዱ መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስ​ደ​ብህ ነው” አለው።


ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው።


ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው


Follow us:

Advertisements


Advertisements