Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከእነርሱ ዘንድ አንዳንዶች ግን፦ “በብዔልዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንዳንዶች ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል ነው፤” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዱ፦ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 11:15
11 Cross References  

ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ።


አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


ሕዝ​ቡም፥ “ጋኔን አለ​ብ​ህን? ማን ሊገ​ድ​ልህ ይሻል?” ብለው መለ​ሱ​ለት።


ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ድዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements