ሉቃስ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በዚያም ቤት ተቀመጡ፤ ከእነርሱ የተገኘውንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ ከቤትም ወደ ቤት አትሂዱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ያቀረቡላችሁን ሁሉ እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያ ቤት ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ለሠራተኛ ደመወዝ ይገባዋል፤ ስለዚህ በገባችሁበት ቤት ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ ቈዩ፤ ከቤት ወደ ቤትም አትዘዋወሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ። See the chapter |