Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 10:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከዚ​ህም በኋላ ሄደው ወደ አን​ዲት መን​ደር ገቡ፤ ማርታ የም​ት​ባል አን​ዲት ሴትም በቤቷ ተቀ​በ​ለ​ችው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በጉዞአቸውም ላይ ሳሉ እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መንገዱን ቀጥሎ ወደ አንዲት መንደር ደረሰ፤ በዚያም ማርታ የምትባል አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 10:38
10 Cross References  

እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


እር​ሱም“ምሕ​ረት ያደ​ረ​ገ​ለት ነዋ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ኪ​ያስ አን​ተም ሂድና እን​ዲሁ አድ​ርግ” አለው።


ማርታ ግን ብዙ በማ​ዘ​ጋ​ጀት ትደ​ክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻ​ዬን ስሠራ አያ​ሳ​ዝ​ን​ህ​ምን? ርጃት በላት” አለ​ችው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም።


ይህ ኢያ​ሶ​ንም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በቄ​ሣር ላይ የወ​ን​ጀል ሥራ ይሠ​ራሉ፤ ሌላ ሕግ​ንም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ኢየ​ሱ​ስም ሌላ ንጉሥ ነው” ይላሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements