Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 1:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የነ​ገ​ሩሽ ቃል እን​ደ​ሚ​ሆን የም​ታ​ምኚ አንቺ ብፅ​ዕት ነሽ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ ብፅዕት ናት!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ከጌታ የተነገረላት ቃል እንደሚፈጸም ያመነች ምንኛ ብፅዕት ናት።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 አንቺ ጌታ የተናገረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የተባረክሽ ነሽ!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።

See the chapter Copy




ሉቃስ 1:45
9 Cross References  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስለ አየ​ኸኝ አመ​ን​ህን? ብፁ​ዓ​ንስ ሳያዩ የሚ​ያ​ምኑ ናቸው” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት።


አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።”


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁ​ሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወ​ጡም ኢዮ​ሣ​ፍጥ ቆመና፥ “ይሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፥ ትጸ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ በነ​ቢ​ዩም እመኑ፤ ነገ​ሩም ይቀ​ና​ላ​ች​ኋል” አለ።


እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና።


የባ​ር​ያ​ውን ትሕ​ትና ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና። እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትው​ልድ ሁሉ ብፅ​ዕት ይሉ​ኛል።


በአ​ገ​ል​ጋዩ በኤ​ል​ያ​ስም ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም፤ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አል​ጐ​ደ​ለም።


እን​ዲ​ሁም ከእ​ርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእ​ር​ስ​ዋና ከል​ጆ​ችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነ​ር​ሱም ማድ​ጋ​ዎ​ቹን ወደ እር​ስዋ ያቀ​ር​ቡ​ላት ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ለ​ብጥ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements