Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 1:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እነሆ፤ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተ እርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርሷ ደግሞ በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷም ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እንኳ መኻን ስትባል ኖራ አሁን በስተእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ ከፀነሰችም እነሆ፥ ስድስተኛ ወርዋ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 1:36
10 Cross References  

በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ።


መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር የለ​ምና”።


ሦራም መካን ነበ​ረች፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተ​ባለ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይም ነበ​ረ​ቻት።


ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር።


ሣራም ፀነ​ሰች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ና​ገ​ረው ወራት ለአ​ብ​ር​ሃም በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት።


ከዚ​ያም በኋላ ሴቲቱ ፀነ​ሰች፥ በዓ​መ​ቱም ኤል​ሳዕ በነ​ገ​ራት ወራት ወንድ ልጅ ወለ​ደች።


ለመ​ፅ​ነስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ው​ለ​ድም ጊዜ አለው፤ ለመ​ኖር ጊዜ አለው፥ ለመ​ሞ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ት​ከል ጊዜ አለው፥ የተ​ተ​ከ​ለ​ው​ንም ለመ​ን​ቀል ጊዜ አለው።


ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements