Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ስለ ሕዝቡ የሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥ በሬ​ው​ንና አው​ራ​ውን በግ አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ረጨው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አሮንም ስለ ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የቀረቡትን በሬውንና አውራ በጉን ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት የሚቀርበውን በሬውንና አውራውን በግ አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በሬውንና የበግ አውራውን ዐርዶ ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በማድረግ አቀረበ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ተቀብሎ ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስለ ሕዝቡ የሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት በሬውንና አውራውን በግ አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው፤

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 9:18
7 Cross References  

ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን።


እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን!


የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements