Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ።።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከመንጋውም እንከን የሌለበትን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አውራ በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያምጣ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለበደሉም ማስተስረያ ምንም ነውር የሌለበት አንድ ተባዕት በግ ወይም በታወቀው ተመን የተተመነውን ገንዘብ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 6:6
8 Cross References  

“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።


ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በሰ​ቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ከመ​ን​ጋው ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ሳያ​ውቅ ስለ ሳተው ስሕ​ተት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ካህ​ኑም አን​ዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​የ​ዋል።


ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይፈቱ ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡ፤ ስለ በደ​ላ​ቸ​ውም ከመ​ን​ጋው አንድ አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ።


በየ​ዓ​መ​ቱም የመ​ሬ​ታ​ች​ንን እህል ቀዳ​ም​ያት፥ የሁሉ ዓይ​ነት ዛፍ የፍሬ ቀዳ​ም​ያት ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እና​መጣ ዘንድ፥


ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements