Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በግ ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች የመጀመሪያውን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “እርሱም ጠቦትን ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት ሌላውን ደግሞ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለጌታ ያመጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ጠቦትን ለማምጣት ገንዘቡ ያልበቃ እንደ ሆነ፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 5:7
24 Cross References  

ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤


አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ዪ​ቱ​ንም ከእ​ህል ቍር​ባን ጋር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ነ​ጻው ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ስለ እርሱ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ቡ​ለት ዘንድ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ በግ ይው​ሰድ።


ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ስለ ፈሳ​ሽዋ ርኩ​ስ​ነት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፦ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ልን፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ዓመት የሆ​ና​ቸ​ውን ጥጃና ጠቦ​ትን፥


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና


“የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች።


በእጁ ከአ​ለው ከዋ​ኖ​ሶች ወይም ከር​ግብ ግል​ገ​ሎች አን​ዱን ያቀ​ር​ባል።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለ​ማ​ወቅ ሰው ከሚ​ሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ የሠ​ሩት ቢኖር፥


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤


ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ በሬ​ሳም የተ​ነሣ ኀጢ​አት ሠር​ቶ​አ​ልና ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ በዚ​ያም ቀን ራሱን ይቀ​ድ​ሰ​ዋል።


ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements