Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገ​ሩም ከማ​ኅ​በሩ ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፉ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘መላው የእስራኤል ሕዝብ ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ አታድርጉ ብሎ እግዚአብሔር ካዘዘውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፣ ይህ ሕዝብ ጥፋቱ ባይታወቀውም በደለኛ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከጉባኤው ፊት ቢሸሸግ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ሠርተው ቢበድሉ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ባለማወቅ ኃጢአት የሠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ቢሆንና፥ ጉዳዩም ከማኅበረሰቡ ቢሰወር፥ ይህም ኃጢአት እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን በማፍረስ በደለኞች ቢያደርጋቸው፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከጉባኤው ፊት ቢሸሸግ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፉ፥

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 4:13
17 Cross References  

“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


አሁ​ንም ሳይ​ገ​ባው ይህን ኅብ​ስት የበላ፥ ይህ​ንም ጽዋ የጠጣ የጌ​ታ​ችን ሥጋ​ውና ደሙ ስለ​ሆነ ዕዳ አለ​በት።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይፈቱ ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡ፤ ስለ በደ​ላ​ቸ​ውም ከመ​ን​ጋው አንድ አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ።


ሕዝቡ በድ​ለ​ዋል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሰ​ዋል፤ እርም ከሆ​ነ​ውም ነገር ሰር​ቀው ወሰዱ፤ በዕ​ቃ​ቸ​ውም ውስጥ ሸሸ​ጉት።


እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥


ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለት የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ በግ ይው​ሰድ።


“ብት​በ​ድ​ሉም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥


በዚ​ያም ቀን አለ​ቃው ለራ​ሱና ለሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ያቅ​ርብ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements