Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መሥዋዕት አቅራቢው ሰው መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 3:2
23 Cross References  

“ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በር ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አስ​ቀ​ድሞ ልጁን አስ​ነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ከክ​ፋ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​መ​ለሱ ይባ​ር​ካ​ችሁ ዘንድ ላከው።”


የሕ​ይ​ወ​ትን ባለ​ቤት ግን ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


ሙሴም ለቅ​ድ​ስና የሚ​ሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ፤


በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


ወይ​ፈ​ኑ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታር​ደ​ዋ​ለህ።


አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።


ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ባሉ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥


እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያር​ደ​ዋል፤ ካህ​ና​ቱም የአ​ሮን ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


ነገር ግን የላ​ሞ​ቹን በኵ​ራት፥ ወይም የበ​ጎ​ቹን በኵ​ራት፥ የፍ​የ​ሎ​ች​ንም በኵ​ራት አት​ቤ​ዥም፤ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፤ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ ስባ​ቸ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ።


“አን​ደ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጭ​ናሉ።


“ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አውራ በግ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያ​ርድ፥ በሰ​ፈሩ ውስጥ ወይም ከሰ​ፈሩ ውጭ ቢያ​ር​ደው፥


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የተ​መ​ረጠ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ያደ​ር​ገው ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባያ​መ​ጣው፥ በሌ​ላም ቦታ ቢያ​ር​ደው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ባያ​መ​ጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈ​ጠ​ር​በ​ታል፤ ደም አፍ​ስ​ሶ​አ​ልና፤ ያም ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements