Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው እህ​ልህ መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ቀ​ርብ በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰና የተ​ፈ​ተገ የእ​ህል እሸት ታቀ​ር​ባ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘የእህል በኵራት ቍርባን ለእግዚአብሔር በምታመጣበት ጊዜ፣ የተፈተገና በእሳት የተጠበሰ እሸት አቅርብ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ከበኵራትም የእህል ቁርባን ለጌታ የምታቀርብ ከሆነ፥ በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸትን የበኵራትህ የእህል ቁርባን አድርገህ ታቀርባለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የመከር ወራት መጀመሪያ የሆነውን በኲራት በምታቀርብበትም ጊዜ ተጠብሶ የታሸ እሸት ይሁን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከበኵራትም የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ብታቀርብ ስለዚህ ቍርባን በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸት ታቀርባለህ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 2:14
16 Cross References  

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ መከ​ሩ​ንም ባጨ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ የእ​ና​ን​ተን መከር በኵ​ራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ ቍር​ባ​ኔን፥ መባ​ዬ​ንና የበጎ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ቴን በበ​ዓ​ላት ቀኖች ታቀ​ር​ቡ​ልኝ ዘንድ ጠብቁ።


አንድ ሰውም ከቤ​ት​ሣ​ሪሳ ከእ​ህሉ ቀዳ​ም​ያት፥ ሃያ የገ​ብስ እን​ጀራ፥ የእ​ህ​ልም እሸት በአ​ቁ​ማዳ ይዞ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም አገ​ል​ጋ​ዩን፥ “ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


ካህ​ኑም ከበ​ኵ​ራቱ ኅብ​ስት፥ ከሁ​ለ​ቱም ጠቦ​ቶች ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለቍ​ር​ባን ያቅ​ር​በው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ፈንታ ነው፤ ላቀ​ረ​በው ለካ​ህኑ ይሁን።


የም​ስ​ጋ​ና​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስት​ሠዉ እን​ዲ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ሠዉ​ለት።


ከብዙ ቀን በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ ቃየል ከም​ድር ፍሬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ፤


ዘይ​ትም ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ ዕጣ​ንም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ህል ቍር​ባን ነው።


ካህ​ኑም ከተ​ፈ​ተ​ገው እህል፥ ከዘ​ይ​ቱም ወስዶ ከዕ​ጣኑ ጋር መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


የስ​ን​ዴም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ይሁን፤ የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን የወ​ይን ጠጅ የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ ይሁን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements