Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ እርሾ አይ​ሁ​ን​በት፤ እርሾ ያለ​በት ነገር፥ ማርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ አታ​ቀ​ር​ቡ​ምና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘ለእግዚአብሔር በእሳት በምታቀርቡት ቍርባን ውስጥ እርሾ ወይም ማር ጨምራችሁ ማቃጠል ስለማይገባችሁ፣ በምታቀርቡት በማንኛውም የእህል ቍርባን እርሾ አይኑርበት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው መባ ጋር የሚገኘውን እርሾም ሆነ ማር. በእሳት ማቃጠል ስለሌለብህ፥ ለእግዚአብሔር የምታቀርበው የእህል መባ ሁሉ ምንም ዐይነት እርሾ ያልነካው ይሁን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሾ ያለበት ነገር ማርም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 2:11
19 Cross References  

ጥቂት እርሾ ብዙ​ውን ዱቄት መጻጻ ያደ​ር​ገው የለ​ምን?


በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የበ​ዓ​ሌም ስብ እስ​ኪ​ነጋ አይ​ደር።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


እርሱም “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።


ልጄ ሆይ፥ ማር ብላ፥ ወለላ ጕሮሮህን ያጣፍጥልህ ዘንድ መልካም ነውና።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ፤” አላቸው።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር።


ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ለ​ዋ​ለህ፤ በመ​ሥ​ዊ​ያ​ውም ላይ ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ እርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements