Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሚቀርበውን መሥዋዕት ከመሠዊያው በስተሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ካህናቱ የአሮን ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ሁሉ ይርጩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በመሠዊያውም አጠገብ በስተ ሰሜን በኩል በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርሱንም ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በመሠዊያውም አጠገብ በሰሜን ወገን በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 1:11
12 Cross References  

በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይ​ን​ህን ወደ ሰሜን መን​ገድ አንሣ” አለኝ። ዐይ​ኔ​ንም ወደ ሰሜን መን​ገድ አነ​ሣሁ፤ እነ​ሆም በመ​ሠ​ዊ​ያው በር በሰ​ሜን በኩል በመ​ግ​ቢ​ያው ይህ የቅ​ን​ዓት ምስል ነበረ። ከዚ​ያም ወደ ምሥ​ራቅ ያስ​ገ​ባል።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት በግ በዚያ ያር​ዱ​ታል፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገበ​ታ​ውን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ ከመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ በድ​ን​ኳኑ በመ​ስዕ በኩል አኖ​ረው፤


ሙሴም የደ​ሙን እኵ​ሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደ​ረ​ገው፤ የደ​ሙ​ንም እኵ​ሌታ በመ​ሠ​ዊ​ያው ረጨው።


እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት እን​ስ​ሳ​ትን በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ፍየ​ል​ዋን ያር​ዳ​ታል።


ሙሴም ያን በግ አረ​ደው፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ረጨው።


የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ዱ​በት በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ጠቦ​ቱን ያር​ዱ​ታል፤ የበ​ደሉ መሥ​ዋ​ዕት ለካ​ህኑ እን​ደ​ሚ​ሆን፥ እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ነውና፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ፥ ደሙ​ንም ይረ​ጩ​በት ዘንድ በሚ​ሠ​ሩ​በት ቀን የመ​ሠ​ዊ​ያው ሕግ ይህ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements