Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ይሁዳ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋራ በተከራከረ ጊዜ፣ “ጌታ ይገሥጽህ” አለው እንጂ የስድብ ቃል በመናገር ሊከስሰው አልደፈረም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ሲናገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊያመጣበት አልደፈረም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ አስከሬን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ “ጌታ ይገሥጽህ” አለው እንጂ የስድብ ቃል አልተናገረም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።

See the chapter Copy




ይሁዳ 1:9
16 Cross References  

እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ሰይጣን ሆይ፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዚአብሔር ይገሥጽህ፣ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን? አለው።


ዳሩ ግን መላእክት በኀይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ፥ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።


በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፤


በቤተ ፌጎ​ርም አቅ​ራ​ቢያ በና​ባው ምድር ቀበ​ሩት፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃ​ብ​ሩን ማንም የሚ​ያ​ውቅ የለም።


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ ክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤


የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና “ዋ! ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ዳዊ​ትም ሊገ​ና​ኛ​ቸው ወጥቶ፥ “በሰ​ላም ወደ እኔ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእ​ና​ንተ ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ለጠ​ላ​ቶቼ አሳ​ል​ፋ​ችሁ ልት​ሰ​ጡኝ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለ​ብ​ኝ​ምና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ይመ​ል​ከ​ተው፥ ይፍ​ረ​ደ​ውም፤” አላ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements