ኢያሱ 9:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በዚያችም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር ለሆነው መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ ዕንጨት ቈራጮችና ውሃ ቀጂዎች አደረጋቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 በዚያም ቀን ኢያሱ በመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለማኅበሩና ለጌታ መሠዊያ እንጨት ቈራጮች ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ነገር ግን በዚሁ ጊዜ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለእስራኤል ሕዝብና ለእግዚአብሔር መሠዊያ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። እነርሱም እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ቦታ፥ ይህንኑ አገልግሎት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 በዚያም ቀን ኢያሱ ለማኅበሩ በመረጠውም ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮች ውኃም ቀጂዎች አደረጋቸው። See the chapter |