Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነ​ዚ​ህም የጠጅ ረዋ​ቶች አዲ​ሶች ሳሉ ሞላ​ን​ባ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ አር​ጅ​ተው ተቀ​ድ​ደ​ዋል፤ መን​ገ​ዳ​ች​ንም እጅግ ስለ ራቀ​ብን እነ​ዚህ ልብ​ሶ​ቻ​ች​ንና ጫማ​ዎ​ቻ​ችን አር​ጅ​ተ​ዋል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነዚህ የወይን ጠጅ አቍማዳዎቻችን ያን ጊዜ ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን እንዴት እንደ ተቀዳደዱ ተመልከቱ፤ ልብሳችንና ጫማችንም ብዙ መንገድ በመጓዛችን ዐልቀዋል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነዚህም የወይን ጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል፤ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነዚህንም የወይን አቁማዳዎች በሞላናቸው ጊዜ ገና አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን የተቀደዱ መሆናቸውን ተመልከቱ! ከጒዞው ርቀት የተነሣ እነሆ፥ ልብሳችንም ጫማችንም አልቆአል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፥ እነሆም፥ ተቀድደዋል፥ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።

See the chapter Copy




ኢያሱ 9:13
8 Cross References  

በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”


እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ።


ወደ እና​ንተ ለመ​ም​ጣት በተ​ነ​ሣ​ን​በት ቀን ይህን እን​ጀራ ትኩ​ሱን ለስ​ንቅ ከቤ​ታ​ችን ያዝ​ነው፤ አሁ​ንም እነሆ፥ ደር​ቆ​አል፤ ሻግ​ቶ​አ​ልም።


አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።


አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ መራ​ችሁ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁም አላ​ረ​ጀ​ባ​ች​ሁም፤ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ላይ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።


በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ጉት ጫማ ያረ​ጀና ማዘ​ቢ​ያው የተ​በ​ጣ​ጠሰ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስ​ን​ቅም የያ​ዙት እን​ጀራ ሁሉ የደ​ረቀ፥ የሻ​ገ​ተና የተ​በ​ላሸ ነበረ።


በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።”


አዲስ ጠጅ​ንም በአ​ሮጌ ረዋት የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ ወይ​ኑም ይፈ​ስ​ሳል፤ ረዋ​ቱም ይቀ​ደ​ዳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements