Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የጋይንም ንጉሥ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ሬሳውንም እስኪመሽ ድረስ እዚያው እንዳለ ተወው፤ ፀሓይ ስትጠልቅም፣ ኢያሱ ሬሳውን እንዲያወርዱትና በከተማው በር ላይ እንዲጥሉት አዘዘ፤ የትልልቅ ድንጋይ ቍልልም ከመሩበት፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ እዚያው ይገኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የዐይንም ከተማ ንጉሥ በእንጨት ላይ ሰቅሎ ሬሳው እስከ ማታ ተንጠልጥሎ እንዲቈይ አደረገ። ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ሬሳው ከተሰቀለበት እንጨት ላይ ወርዶ በከተማይቱ ቅጽር በር መግቢያ እንዲጣል አደረገ፤ በእርሱም ላይ ብዙ የድንጋይ ቊልል ከመሩበት፤ የድንጋዩም ቊልል እስከ አሁን በዚያው ይገኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፥ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 8:29
14 Cross References  

አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።


በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ተመ​ለሰ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜ​ቃ​ኮር ተብሎ ተጠራ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።


ለሚ​ፈ​ሩት ምግ​ብን ሰጣ​ቸው፤ ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያስ​ባል።


በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በል​ብና ንጉሥ አደ​ረገ።


አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።


የኢ​ያ​ሪኮ ንጉሥ፥ በቤ​ቴል አጠ​ገብ ያለ​ችው የጋይ ንጉሥ፥


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ ሳይ​ሞት ይዘው ወደ ኢያሱ አመ​ጡት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements