Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነሡ፤ ኢያ​ሱም እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ ወጡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዋም ገብ​ተው ያዙ​አት፤ ፈጥ​ነ​ውም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይህን እንዳደረገም ያደፈጡት ሰዎች ከተደበቁበት ስፍራ በፍጥነት ወጥተው ወደ ፊት ሮጡ፤ ገብተው ከተማዪቱን ያዟት፤ ወዲያውኑም በእሳት አቃጠሏት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የተደበቁትም ፈጥነው ከስፍራቸው ተነሡ፥ ኢያሱም እጁን በዘረጋ ጊዜ ሮጡ፥ ወደ ከተማይቱም ገብተው ያዙአት፤ ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እጁንም በዘረጋ ጊዜ ሸምቀው የነበሩት ወታደሮች ከቦታቸው ተነሥተው ወደፊት ሄዱ፤ ወደ ከተማዋም በፍጥነት ገብተው በቊጥጥራቸው ሥር አደረጓትና ወዲያውኑ አቃጠሉአት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የተደበቁትም ፈጥነው ከስፍራቸው ተነሡ፥ ኢያሱም እጁን በዘረጋ ጊዜ ሮጡ፥ ወደ ከተማይቱም ገብተው ያዙአት፥ ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 8:19
5 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።


የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነ​ሥ​ተው በበ​ዓ​ል​ታ​ምር ተዋጉ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አድ​ፍ​ጠው የነ​በ​ሩት ከስ​ፍ​ራ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ምዕ​ራብ ወጡ።


ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም ፈጥ​ነው ወደ ገባ​ዖን ሮጡ፤ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩ​ትም መጥ​ተው ከተ​ማ​ውን ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ።


በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements