Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በጋ​ይና በቤ​ቴ​ልም ውስጥ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ሳ​ደድ ያል​ወጣ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከፍ​ተው ተዉ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ደ​ዱት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እስራኤልን ለማሳደድ ከጋይና ከቤቴል ያልወጣ ወንድ አልነበረም፤ ከተማዪቱንም ከፍተው ትተው እስራኤልን ማሳደድ ያዙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፤ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዐይ ወይም በቤትኤል የሚገኝ ሰው ሁሉ ወጥቶ እስራኤላውያንን ሲያሳድድ ከተማይቱ ባዶዋን ክፍት ሆና ቀረች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፥ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 8:17
9 Cross References  

ጠቢ​ባ​ን​ንም በተ​ን​ኰ​ላ​ቸው ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ምክ​ርን የሚ​ጐ​ነ​ጉኑ ሰዎ​ችን አሳብ ያጠ​ፋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።


ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው።


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።


የሀ​ገ​ሪ​ቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲ​ርቁ አደ​ረ​ጓ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements