Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 6:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚ​ያ​ችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህ​ችን ከተማ ኢያ​ሪ​ኮን ለመ​ሥ​ራት የሚ​ነሣ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠ​ረ​ቷን በበ​ኵር ልጁ የሚ​ጥል፥ በሮ​ች​ዋ​ንም በታ​ናሹ ልጁ የሚ​ያ​ቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህች ከተማ ኢያሪኮን መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤ “መሠረቷን ሲጥል፣ የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣ የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ኢያሱ፦ “ይህቺን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሣ የተረገመ ይሁን፤ መሠረቱን ሲጥል የበኲር ልጁ ይጥፋ፤ መዝጊያውን ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ፤” ብሎ ረገመ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ፦ ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፥ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ ብሎ ማለ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 6:26
9 Cross References  

በእ​ር​ሱም ዘመን የቤ​ቴል ሰው አኪ​ያል ኢያ​ሪ​ኮን ሠራ፤ በነ​ዌም ልጅ በኢ​ያሱ ቃል እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ በበ​ኵር ልጁ በአ​ቢ​ሮን መሠ​ረ​ቷን አደ​ረገ፥ በታ​ናሹ ልጁም በዜ​ጉብ በሮ​ች​ዋን አቆመ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም አስ​ማት እያ​ደ​ረጉ የሚ​ዞሩ ሰዎች ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስት ባሉ​ባ​ቸው ላይ “ጳው​ሎስ በሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ር​በት በኢ​የ​ሱስ ስም እና​ም​ላ​ች​ኋ​ለን” እያሉ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ስም ይጠ​ሩ​ባ​ቸው ነበር።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።


ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እው​ነት ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።


ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢያ​ሪኮ ልኮ​ኛ​ልና፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው።


ከኢ​ያ​ኖ​ክም ወደ መአ​ኮና፥ ወደ አጣ​ሮ​ትም፥ ወደ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ፋል፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ይገ​ባል፥ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ይወ​ጣል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements