Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሰባ​ቱም ካህ​ናት ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ቱ​ንም ይነፉ ነበር፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም በፊ​ታ​ቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እየሄዱ፣ መለከቱን ባለማቋረጥ ይነፉ ጀመር፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም እነዚህን በመቅደም ሲሄዱ፣ የደጀን ጠባቂዎቹ ደግሞ የእግዚአብሔርን ታቦት ይከተሉ ነበር፤ ካህናቱም ሳያቋርጡ መለከት ይነፉ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በጌታ ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፤ ተዋጊዎቹም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፤ የኋላ ደጀንም የሆነው ሕዝብ ከጌታ ታቦት በኋላ ይመጡ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሰባቱን እምቢልታ የያዙት ሰባት ካህናት እምቢልታቸውን ሳያቋርጡ እየነፉ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ለፊት ሄዱ፤ መለከቱ ሳያቋርጥ እየተነፋ ወታደሮቹ ከካህናቱ ቀድመው ሌላው ሕዝብ ደግሞ ከታቦቱ በኋላ ይከተል ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፥ ሰልፈኞቹም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፥ የቀሩትም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ታቦት በኋላ ይመጡ ነበር፥ ካህናቱም እየሄዱ ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር።

See the chapter Copy




ኢያሱ 6:13
8 Cross References  

በጎ ሥራ መሥ​ራ​ትን ቸል አን​በል፥ በጊ​ዜው እና​ገ​ኘ​ዋ​ለ​ንና።


እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ኪዳን ታቦት የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ረ​ታ​ቸው ጊዜ ሰባት በሬ​ዎ​ች​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ሠዉ።


ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ።


ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።


ሰል​ፈ​ኞ​ችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ነጋ​ሪት ይመቱ ነበር፤ ከታ​ቦቱ በኋላ ይከ​ተሉ የነ​በ​ሩ​ትም ቀንደ መለ​ከ​ቱን እየ​ነፉ ይሄዱ ነበር።


ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የቀ​ረው ሕዝብ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ፤ ስድ​ስት ቀንም እን​ዲህ አደ​ረጉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements