Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢያሱ እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዮር​ዳ​ኖ​ስን አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እንደ አዘ​ዘው በእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ቍጥር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮች አን​ሥ​ተው ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወሰዱ፤ በዚ​ያም አኖ​ሩ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እስራኤላውያንም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረውም መሠረት፣ በእስራኤል ነገዶች ቍጥር ልክ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል አነሡ፤ ወደ ሰፈራቸውም ይዘው በመሻገር በዚያ አኖሯቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፤ ጌታም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቍጥር ከዮርዳኖስ መካከል ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሰዎቹም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረው መሠረት በእስራኤል ነገዶች ቊጥር ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወደ ሰፈሩበት ቦታ ወስደው አስቀመጡ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፥ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 4:8
6 Cross References  

ኢያ​ሱም ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ዐሥራ ሁለ​ቱን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ል​ገላ አቆ​ማ​ቸው።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements