Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚያም ቀን ጌታ ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም ይፈሩት እንደ ነበር እንዲሁ ኢያሱን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ፈሩት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚያን ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሙሴን ያከብሩት እንደ ነበር ኢያሱንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አከበሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፥ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 4:14
14 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር መሆ​ኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደ​ር​ግህ ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ።


ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።


አንተ ሥራ​ህን ታሳ​ምር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ናቸ​ውና። ክፉ ብታ​ደ​ርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታ​ጠ​ቁም ለከ​ንቱ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ለመ​ቅ​ጣት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና።


ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ላከ፤ ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሳሙ​ኤ​ልን እጅግ ፈሩ​አ​ቸው።


እስ​ራ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ታላ​ቂ​ቱን እጅ አዩ፤ ሕዝ​ቡም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አመኑ፤ ባሪ​ያ​ው​ንም ሙሴን አከ​በሩ።


ሁሉ​ንም ሙሴ በደ​መ​ናና በባ​ሕር አጠ​መ​ቃ​ቸው።


አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ለሕ​ዝቡ ሞገ​ስን ሰጠ፤ አዋ​ሱ​አ​ቸ​ውም፤ ይህ ሙሴም በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና በፈ​ር​ዖን፥ በሹ​ሞ​ቹም ፊት እጅግ የከ​በረ ሰው ነበረ።


በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በ​ሩት የነ​ቢ​ያት ልጆች ኤል​ሳዕ ወደ እነ​ርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤ​ል​ያስ መን​ፈስ በኤ​ል​ሳዕ ላይ ዐር​ፎ​አል” አሉ። ሊገ​ና​ኙ​ትም መጥ​ተው በፊቱ በም​ድር ላይ ሰገ​ዱ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements