Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አርባ ሺሕ ያህሉ ጦርና ጋሻቸውን ይዘው፣ ለውጊያ ዝግጁ ሆነው፣ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አርባ ሺህ ያህል ሰዎች መሣርያ ታጥቀው ለጦርነት በጌታ ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከእነርሱም የተውጣጡ ብዛታቸው አርባ ሺህ ያኽል የሆነ ጦረኞች በእግዚአብሔር ፊት ተሰልፈው በኢያሪኮ አቅራቢያ ወደሚገኘው ሜዳ ተሻገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለሰልፍ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 4:13
11 Cross References  

የሰ​ይ​ጣ​ንን ተን​ኰል መቋ​ቋም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ልበሱ።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ታ​ተ​ሉት፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ሜዳ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ያዙ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ተበ​ት​ነው ነበር።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ተከ​ታ​ተ​ላ​ቸው፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም በኢ​ያ​ሪኮ ሜዳ አገ​ኙት፤ ይዘ​ውም በሐ​ማት ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ዴብ​ላታ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አመ​ጡት፤ እር​ሱም ፍር​ድን በእ​ርሱ ላይ ተና​ገረ።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ንጉ​ሡን ተከ​ተሉ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በኩል ባለው ሜዳ ያዙት፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ከእ​ርሱ ተለ​ይ​ተው ተበ​ት​ነው ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።


እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ።


“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።


ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements