Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት፣ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእስራኤላውያን ፊት ቀድመው ተሻገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከሮቤልና ከጋድ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለጦርነት የተዘጋጁት ሰዎች ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት ከሕዝቡ ግንባር ቀደም ሆነው ተሻገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 4:12
9 Cross References  

ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።


የይ​ሁዳ ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥


እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ።


“በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።


በዚያ ከሕ​ዝቡ ገዦች ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የአ​ለ​ቆች ምድር እንደ ተከ​ፈ​ለች፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ፍሬ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽድ​ቁን፥ ፍር​ዱ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር አደ​ረገ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ።


አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements