Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሕዝቡንም እንዲህ ሲሉ አዘዙ፤ “ሌዋውያን ካህናቱ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ፣ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ታቦቱን ተከተሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦ “የአምላካችሁን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦቱንና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ እርሱን በመከተል፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።

See the chapter Copy




ኢያሱ 3:3
20 Cross References  

ሙሴም ይህ​ችን ሕግ ጻፈ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ይሸ​ከሙ ለነ​በ​ሩት ለሌዊ ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰጣት።


ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሰባት መሰ​ንቆ የሚ​መቱ ክፍ​ሎች ነበሩ። በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን ይሠዉ ነበር።


አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


አንድ ጸሐፊም ቀርቦ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ።


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


በእ​ና​ን​ተና በታ​ቦቱ መካ​ከል ያለው ርቀት በስ​ፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መን​ገድ በፊት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ት​ምና የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ትን መን​ገድ እን​ድ​ታ​ውቁ ወደ ታቦቱ አት​ቅ​ረቡ።”


ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር የነ​በ​ረ​ውን የወ​ርቅ ዕቃ ያለ​በ​ትን ሣጥን አወ​ረዱ፤ በታ​ላ​ቁም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ሩት፤ በዚ​ያም ቀን የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements