Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 24:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ኢያሱ ባለ​በት ዘመን ሁሉ፥ ከኢ​ያ​ሱም በኋላ በነ​በ​ሩት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ፥ እስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ለኩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ከኢያሱም በኋላ በሕይወት በኖሩትና እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ በሚያውቁት ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ኢያሱ በኖረበት ዘመን ሁሉ፥ ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የጌታን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ፥ እስራኤል ጌታን አገለገሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን አመለኩ፤ ከእርሱም ሞት በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ በዐይናቸው ያዩት ሽማግሌዎች እስከ ኖሩበት ዘመን ድረስ እርሱኑ በማምለክ ኖሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ኢያሱ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ፥ እስራኤል እግዚአብሔርን አመለኩ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 24:31
13 Cross References  

ኢያ​ሱም በነ​በ​ረ​በት ዘመን ሁሉ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ቁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት፥ ከኢ​ያሱ በኋላ በነ​በሩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።


የማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ሄ​ዱ​ባት ምድር በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይስሙ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ይማሩ።”


ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”


ዛሬ ልጆ​ቻ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተግ​ሣጽ፥ ታላ​ቅ​ነ​ቱ​ንም፥ የጸ​ና​ችም እጁን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክን​ዱን፥ ያዩና ያወቁ እን​ዳ​ይ​ደሉ ዕወቁ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ።


ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።


ኢዮ​አ​ስም በካ​ህኑ በኢ​ዮ​አዳ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ጋ​ቸ​ውን ታላ​ላቅ ሥራ​ዎች ሁሉ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋ​ልና።


ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ።


ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን ባሰ​ና​በተ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድ​ሪ​ቱን ሊወ​ርሱ ወደ​የ​ር​ስ​ታ​ቸው ገቡ።


ትው​ልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ተጨ​መሩ፤ ከእ​ነ​ዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ያላ​ወቀ ሌላ ትው​ልድ ተነሣ።


ኢዮ​ስ​ያ​ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩ​ሱን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ልኩ አደ​ረገ። በዘ​መኑ ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቁም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements