Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድ​ዱት ዘንድ ለራ​ሳ​ችሁ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለመውደድ ተጠንቀቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታን አምላካችሁንም የምትወድዱ መሆናችሁን እጅግ በጥንቃቄ አስተውሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን የምትወዱ መሆን እንደሚገባችሁ በጥንቃቄ አስቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱት ዘንድ ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 23:11
17 Cross References  

ብቻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ታደ​ርጉ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትወ​ድዱ ዘንድ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ችሁ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።


አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር።


ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።


ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ አም​ላክ ነኝና።


እን​ግ​ዲህ እንደ ዐዋ​ቂ​ዎች እንጂ እንደ አላ​ዋ​ቂ​ዎች ሳይ​ሆን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ላ​ለሱ በጥ​ን​ቃቄ ዕወቁ።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ብት​ጠጉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ብት​ጋቡ፥ እና​ን​ተም ወደ እነ​ርሱ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ ብት​ደ​ራ​ረሱ፥


ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ብት​ሰማ፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብት​ወ​ድድ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም ሁሉ ብት​ሄድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ብት​ጠ​ብቅ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ፤ በቍ​ጥ​ርም ትበ​ዛ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ሄ​ድ​ባት በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements