Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ወንድሞቻችሁን አሳርፏቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ ርስት አድርጎ በሰጣችሁ ምድር ወዳለው ቤታችሁ ተመለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንግዲህ አሁን አምላካችሁ ጌታ እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ ስለዚህ አሁን ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የጌታ ባርያ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነሆ አሁን አምላካችሁ እግዚአብሔር በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ሰላምን ሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ወደ ሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ወደሚገኘውና ርስት አድርጋችሁ ወደ ወረሳችሁት ምድር ተመልሳችሁ ሂዱ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፥ አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:4
16 Cross References  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴም እንደ ሰጣ​ቸው ከእ​ርሱ ከም​ናሴ ጋር የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤


ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።


ሙሴም ለሮ​ቤል ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ማረ​ፊ​ያና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና።


ኢያሱ አሳ​ር​ፎ​አ​ቸው ቢሆን ኖሮስ፥ ከብዙ ዘመን በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባል​ተ​ና​ገ​ረም ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፥ አሳ​ር​ፍ​ህ​ማ​ለሁ” አለው።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።”


ይህ​ንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቃ​ች​ኋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።


“አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ምን? በም​ድ​ርም የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሕ​ዝቡ ፊት ተገ​ዝ​ታ​ለ​ችና በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ከአሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ዕረ​ፍ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements