Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 22:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ወገኖች የሚኖሩበትን አገር በጦርነት ለማጥፋት የመሄድን ነገር አላነሡም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች ጌታን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ለማጥፋት ወጥተን እንወጋታለን ብለው አልተናገሩም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እስራኤላውያንም በመልሱ ረክተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም በኋላ የሮቤልና የጋድ ሕዝብ የሚኖሩባትን ምድር ለመደምሰስ ጦርነት ስለ ማንሣት ጉዳይ መናገር አልፈለጉም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፥ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው እንዲወጉአቸው አልተናገሩም።

See the chapter Copy




ኢያሱ 22:33
13 Cross References  

እርሱ ደግሞ ተቀ​ብሎ በክ​ንዱ ታቀ​ፈው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነው።


ዳዊ​ትም ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” አላ​ቸው። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፥ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ተን​በ​ር​ክ​ከው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ፤ ደግ​ሞም ለን​ጉሡ።


ካህኑ ፊን​ሐ​ስና የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል መሳ​ፍ​ንት ሁሉ ፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰ​ኛ​ቸው።


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


በመ​ም​ጣቱ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በአ​ጽ​ና​ና​ች​ሁት ማጽ​ና​ና​ትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡና እን​ደ​ም​ት​ቀኑ ፍቅ​ራ​ች​ሁን ነግ​ሮ​ናል፤ ይህ​ንም ሰምቼ ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ በዛ።


እነ​ር​ሱም አን​ብ​በው እጅግ ደስ አላ​ቸው፥ ተጽ​ና​ኑም።


ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲና​ገሩ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን አዳ​መ​ጡ​አ​ቸው።


የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ከእ​ር​ሱም ጋር የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከሮ​ቤል ልጆ​ችና ከጋድ ልጆች፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዘንድ ከገ​ለ​ዓድ ሀገር ወደ ከነ​ዓን ሀገር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ ወሬም አመ​ጡ​ላ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements